ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 95:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።

2. ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤በዝማሬም እናወድሰው።

3. እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።

4. የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።

5. እርሱ ፈጥሮአታልና፣ ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።

6. ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤

7. እርሱ አምላካችን ነውና፤እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

8. በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።

9. ሥራዬን ቢያዩም፣አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።

10. ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤እኔም፣ “ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።

11. ስለዚህ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብዬ፣በቍጣዬ ማልሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 95