ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 95:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።

2. ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤በዝማሬም እናወድሰው።

3. እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።

4. የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።

5. እርሱ ፈጥሮአታልና፣ ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 95