1. በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤
2. እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ልዑል እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።
3. እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያ ስፍራው ይመጣል፤ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል።