ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 2:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ ጠላት ሆናችሁተነሣችሁ፤የጦርነት ሐሳብ ሳይኖራቸው፣በሰላም ከሚያልፉ ሰዎች ላይ፣ማለፊያ መጐናጸፊያ ገፈፋችሁ።

9. ከሚወዱት ቤታቸው፣የሕዝቤን ሴቶች አስወጣችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው፣ለዘላለም ወሰዳችሁ።

10. ተነሡና፤ ከዚያ ሂዱ፤ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ምክንያቱም ረክሶአል፤ክፉኛም ተበላሽቶአል።

11. ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 2