ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 7:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እርሱን ስለ በደልሁ፣እስኪቆምልኝእስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቊጣ እቀበላለሁ፤እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም ጽድቁን አያለሁ።

10. ጠላቴም ታያለች፤ኀፍረትንም ትከናነባለች፤“አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?”ያለችኝን፣ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤አሁንም እንኳ፣እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።

11. ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት፣ድንበራችሁንም የምታሰፉበት ቀን ይመጣል።

12. በዚያ ቀን ሰዎች፣ከአሦር እስከ ግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ፣ከባሕር ወደ ባሕር፣ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ።

13. ከሥራቸው የተነሣ፣በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።

14. ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤እንደ ቀድሞው ዘመን፣በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 7