ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 1:7-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።

8. ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤የእናትህንም ትምህርት አትተው።

9. ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል።

10. ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣እሺ አትበላቸው፤

11. “ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤

12. እንደ መቃብር፣ ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱ፣ከነሕይወታቸው እንዳሉ እንዋጣቸው፤

13. ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በያይነቱ እናገኛለን፤ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤

14. ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤የጋራ ቦርሳ ይኖረናልቃ ቢሉህ፣

15. ልጄ ሆይ፤ አብረሃቸው አትሂድ፤በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤

16. እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው።

17. ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣ምንኛ ከንቱ ነው!

18. እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው።

19. ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 1