እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።