ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 6:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።

11. እነሆ፤ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጥቶአልና፤ታላላቅ ቤቶችን ያወድማቸዋል፤ትንንሾቹንም ያደቅቃቸዋል።

12. ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን?ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን?እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

13. እናንተ ሎዶባርን በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፣“ቃርናይምን በራሳችን ብርታት ይዘናል” የምትሉ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 6