ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 8:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በምድር ላይ ረሐብን የምሰድበት ዘመን ይመጣል፤ይኸውም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሐብ እንጂ፣እንጀራን የመራብ ወይም ውሃን የመጠማት አይደለም።

12. ሰዎች እግዚአብሔርን ለመሻት፣ከባሕር ወደ ባሕር፣ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይንከራተታሉ፤ነገር ግን አያገኙትም።

13. “በዚያ ቀን፣“ቈነጃጅት ሴቶችና ብርቱዎች ጎልማሶች፣ከውሃ ጥም የተነሣ ይዝላሉ።

14. በሰማርያ ኀፍረት የሚምሉ፣ወይም፣ ‘ዳን ሆይ፤ ሕያው አምላክህን’ የሚሉ፣ወይም ‘ሕያው የቤርሳቤህ አምላክን’ ብለው የሚምሉ፣ዳግመኛ ላይነሡ፣ ለዘላለም ይወድቃሉ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 8