ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 1:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ጽዮን በፍትሕ፣በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።

28. ዐመፀኞችና ኀጢአታኞች ግን በአንድነት ይደቃሉ፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።

29. “ደስ በተሰኛችሁባቸው የአድባር ዛፎችታፍራላችሁ፤በመረጣችኋቸውም የአትክልት ቦታዎችትዋረዳላችሁ።

30. ቅጠሉ እንደ ጠወለገ ወርካ፣ውሃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁ።

31. ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፣ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 1