ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 1:6-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጒራችሁጤና የላችሁም፤ቍስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤አልታጠበም፤ አልታሰረም፤በዘይትም አልለዘበም።

7. አገራችሁ ባድማ፣ከተሞቻችሁ በእሳት የተቃጠሉ ይሆናሉ፤ዐይናችሁ እያየ፣መሬታችሁ በባዕድ ይነጠቃል፤ጠፍም ይሆናል።

8. የጽዮን ሴት ልጅበወይን አትክልት ውስጥ እንዳለ ዳስ፣በዱባ ተክል ወስጥ እንደሚገኝ ጐጆ፣እንደ ተከበበም ከተማ ተተወች።

9. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣እንደ ሰዶም በሆንንገሞራንም በመሰልን ነበር።

10. እናንተ የሰዶም ገዦች፤የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።

11. “የመሥዋዕታችሁ ብዛትለእኔ ምኔ ነው?” ይላል እግዚአብሔር።“የሚቃጠለውን የአውራ በግናየሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤በበሬ፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስአልሰኝም።

12. በፊቴ ለመቅረብ ስትመጡ፣ይህን ሁሉ እንድታመጡ፣የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ?

13. ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤የወር መባቻ በዓላችሁን፣ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንናበክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥአልቻልሁም።

14. የወር መባቻችሁንና የተደነገጉ በዓሎቻችሁንነፍሴ ጠልታለች፤ሸክም ሆነውብኛል፤መታገሥም አልቻልሁም።

15. እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤

16. ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 1