ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 10:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!

2. የድኾችን መብት ለሚገፉ፣የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!

3. በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል?ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ?ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ?ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?

4. ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፣ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም።እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

5. “የቍጣዬ በትር ለሆነ፣የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!

6. ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።

7. እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤በልቡም ይህ አልነበረም፤ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።

8. እንዲህም ይል ነበር፤‘የጦር አዛዦቼ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?

9. ካልኖ እንደ ከርከሚሽ፣ሐማት እንደ አርፋድ፣ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደሉምን?

10. የጣዖታትን መንግሥታት፣ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ መንግሥታት የሚበልጡትን እጄ እንደ ያዘች ሁሉ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 10