ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 10:15-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን?መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን?በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።

16. ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳትይለኰሳል።

17. የእስራኤል ብርሃን እሳት፣ቅዱሱም ነበልባል ይሆናል፤በአንድ ቀንምእሾኹንና ኵርንችቱን እሳት ይበላዋል፤

18. ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል።

19. በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ሕፃን ልጅ እንኳ ቈጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል።

20. በዚያን ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፣ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፣ከእንግዲህ ወዲህበመታቸው ላይ አይታመኑም፤ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ፣በእውነት ይታመናሉ።

21. የተረፉት ይመለሳሉ፣ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።

22. እስራኤል ሆይ፤ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፣የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ።ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል።

23. ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል።

24. ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤“በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤ግብፅ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፣በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው።

25. በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤በእነርሱም ላይ መቅሠፍቴን አመጣለሁ።”

26. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደመታ፣በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤በግብፅ እንዳደረገውም ሁሉ፣በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።

27. በዚያን ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ከውፍረትህም የተነሣቀንበሩ ይሰበራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 10