ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 2:11-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።

12. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣የተኵራራውን በሙሉየሚያዋርድበት ቀን አለው።

13. ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፣የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፣

14. ታላላቁን ተራራ ሁሉ፣ከፍ ያለው ኰረብታ ሁሉ፣

15. ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፣የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣

16. የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

17. የሰው እብሪት ይዋረዳል፤የሰውም ኵራት ይወድቃል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤

18. ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።

19. እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱከግርማውም የተነሣ፣ወደ ዐለት ዋሻወደ መሬትም ጒድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።

20. በዚያን ቀን ሰዎችሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውንለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

21. እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱእንዲሁም ከግርማው የተነሣ፣ወደ ድንጋይ ዋሻ፣ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 2