ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 20:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብፅና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደሄደ፣

4. እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብፃውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብፅን ያዋርዳል።

5. በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብፅ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም።

6. በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 20