ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 23:17-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ሰባው ዓመት ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞው የግልሙትና ሥራዋ ተመልሳ፣ በምድር ላይ ካሉት የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር በንግዷ ትገለሙታለች።

18. ያም ሆኖ ትርፏና ያገኘችው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ አይከማችም፤ አይጠራቀምም። ትርፏም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩት የተትረፈረፈ ምግብና ጥሩ ልብስ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 23