ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 23:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖአል።

10. የተርሴስ ልጅ ሆይ፤ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምናእንደ ዐባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።

11. እግዚአብሔር እጁን በባሕር ላይ ዘረጋ፤መንግሥታቷንም አስደነገጠ፤የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ፣ትእዛዝ ሰጠ፤

12. እንዲህም አለ፤ “አንቺ የተቀጠቀጥሽ የሲዶን ድንግል ሆይ!ከእንግዲህ ደስ አይበልሽ፤“ተነሺ ወደ ቆጵሮስ ተሻገሪ፤በዚያም እንኳ ሰላም አታገኚም።”

13. እነሆ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ተመልከቱ፤ሕዝቡ ከንቱ ሆኖአል።አሦራውያን የምድረ በዳ አራዊትመፈንጪያ አደረጓት፤የግንብ ማማቸውን ሠሩባት፤ምሽጎቿን አወደሙ፤የፍርስራሽ ክምር አደረጓት።

14. እናንት የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤ምሽጋችሁ ፈርሶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 23