ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 27:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቃቸው፣የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣በዚያን ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ይህም ኀጢአቱን የማስወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።

10. የተመሸገባት ከተማ ባዶዋን ቀርታለች፤እንደ ምድረ በዳም የተተወች ስፍራ ሆናለች፤ጥጆች በዚያ ይሰማራሉ፤እዚያም ይተኛሉ፤ቅርንጫፎቿንም ልጠው ይበላሉ።

11. ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል።ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ፈጣሪው አይራራለትም፤ያበጀውም አይምረውም።

12. በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ፤ እግዚአብሔር እህሉን ይወቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።

13. በዚያ ቀን ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር የጠፉትና በግብፅ የተሰደዱትም መጥተው፣ በተቀደሰው ተራራ በኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን ያመልካሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 27