ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 62:6-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም።እናንት ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ፈጽሞ አትረፉ፤

7. ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት፣የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ዕረፍት አትስጡት።

8. እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሎአል፤“ከእንግዲህ እህልሽን፣ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።

9. ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴአደባባዮች ይጠጡታል።”

10. ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ፤ድንጋዩን አስወግዱ፤ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።

11. እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ፣እንዲህ ሲል ዐውጆአል፤“ለጽዮን ሴት ልጅ፣‘እነሆ፤ አዳኝሽ መጥቶአል፤ዋጋሽ በእጁ አለ፤ዕድል ፈንታሽም ከእርሱ ጋር ነው’ በሏት።”

12. እነርሱም ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር የተቤዣቸው ተብለው ይጠራሉ፤አንቺም የምትፈለግ፣ከእንግዲህም የማትተው ከተማ ትባያለሽ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 62