ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 9:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።

16. ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።

17. ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረ በትና ክፉ አድራጊ ነው፤የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

18. እንግዲህ ርኵሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤እሾህንና ኵርንችትን ይበላል፤ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ጢሱም ተትጐልጒሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።

19. በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመርማገዶ ይሆናል፤ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።

20. በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤በግራም በኩል ይበላሉ፤ነገር ግን አይጠግቡም፤እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 9