ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 21:15-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ሖሎንን፣ ዳቤርን፣

16. ዐይንን፣ ዮጣንና ቤትሳሚስን ከነ ማሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው።

17. ከብንያም ነገድ ገባዖን፣ ጌባዕ፣

18. ዓናቶትና አልሞን የተባሉትን አራት ከተሞች ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

19. ለካህናቱ ለአሮን ዝርያዎች ከነ ማሰማሪያቸው የተሰጧቸው ከተሞች ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

20. የሌዊ ልጅ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለሌሎቹ ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ላይ ተከፍለው የሚከተሉት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

21. በተራራማው በኤፍሬም ምድርም ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣

22. ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነመሠማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጡአቸው።

23. እንዲሁም ከዳን ነገድ ኤልተቄን፣ ገባቶን፤

24. ኤሎንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው።

25. ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው።

26. እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 21