ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 10:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. “ታዲያ ለምን ከማሕፀን አወጣኸኝ?ምነው ዐይን ሳያየኝ በሞትሁ ኖሮ!

19. ምነው ባልተፈጠርሁ!ወይም ከማሕፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወረድሁ!

20. ጥቂት የሆነው ዘመኔ እያለቀ አይደለምን?ከሥቃዬ ፋታ እንዳገኝ ተወት አድርገኝ፤

21. ወደማልመለስበት ስፍራ፣ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ አገር ከመሄዴ በፊት፣

22. ብርሃኑ እንደ ጨለማ ወደ ሆነበት፣የሞት ጥላ ወዳረበበበት፣ ሥርዐት የለሽ ወደ ሆነ ምድር፣ድቅድቅ ጨለማ ወደ ሰፈነበት አገር ሳልሄድ ተወኝ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 10