ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:15-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ክብሬን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።

16. ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቶአል፤ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፎአል፤

17. ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው።

18. “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!

19. አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል።

20. ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል።

21. ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16