ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር።

6. “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ዝም ብልም አይተወኝም።

7. እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።

8. ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።

9. በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ጥርሱን ነከሰብኝ፤ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።

10. ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤በንቀት ጒንጬን ጠፈጠፉኝ፤በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።

11. እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።

12. በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤

13. የእርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈሳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16