ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 27:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤

2. “ፍትሕ የነሣኝ ሕያው እግዚአብሔርን!ነፍሴንም መራራ ያደረጋት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን!

3. በውስጤ የሕይወት እስትንፋስ፣በአፍንጫዬም ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ እስካለ ድረስ፣

4. ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 27