ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 28:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች።

6. ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል።

7. ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፤የአሞራም ዐይን አላየውም፣

8. ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤አንበሳም በዚያ አላለፈም።

9. ሰው እጁን በቡላድ ድንጋይ ላይ ያነሣል፤ተራሮችንም ከሥር ይገለብጣል።

10. በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።

11. የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 28