ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 29:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እኔም ብርቱ ነበርሁ፤የእግዚአብሔርም ወዳጅነት ቤቴን ይባርክ ነበር፤

5. ሁሉን የሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ነበረ፤ልጆቼም በዙሪያዬ ነበሩ፤

6. መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር።

7. “ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣

8. ጐበዛዝት አይተውኝ ገለል ይሉ፣ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።

9. የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤

10. የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 29