ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 3:11-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. “ምነው ገና ስወለድ በጠፋሁ!ምነው ከማሕፀን ስወጣ በሞትሁ!

12. የሚቀበሉኝ ጒልበቶች፤የሚያጠቡኝ ጡቶች ለምን ተገኙ?

13. ይህን ጊዜ በሰላም በተኛሁ፣አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤

14. አሁን ፈርሶ የሚታየውን ስፍራ ለራሳቸው ካሠሩት፣ከምድር ነገሥታትና ከአማካሪዎች ጋር፣

15. ቤታቸውን በብር ከሞሉ፣ወርቅም ከነበራቸው ገዦች ጋር ባረፍሁ ነበር።

16. ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፣ብርሃንም እንዳላየ ሕፃን በሆንሁ ነበር።

17. በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤

18. ምርኮኞች እንደ ልባቸው ይቀመጣሉ፤ከእንግዲህም የአስጨናቂዎቻቸውን ጩኸት አይሰሙም።

19. ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 3