ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 34:13-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ምድርን እንዲገዛ የሾመው አለን?የዓለምስ ሁሉ ባለቤት ያደረገው ማን ነው?

14. እርሱ መንፈሱን መልሶ ቢወስድ፣እስትንፋሱንም ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣

15. ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።

16. “ማስተዋል ካለህ ይህን ስማ፤እኔ የምለውንም አድምጥ።

17. ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን?አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ?

18. ነገሥታትን ‘የማትረቡ ናችሁ፣’መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’የሚላቸው እርሱ አይደለምን?

19. ሁሉም የእጁ ሥራ ስለሆኑ፣እርሱ ለገዦች አያደላም፤ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።

20. እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።

21. “ዐይኖቹ የሰውን አካሄድ ይመለከታሉ፤ርምጃውንም ሁሉ ይከታተላሉ።

22. ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፣ጨለማ ስፍራ ወይም የሞት ጥላ የለም።

23. ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።

24. ያለ ምንም ጥያቄ ኀያላንን ያንኰታኵታል፤ሌሎችንም በቦታቸው ይሾማል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 34