ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 40:13-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን።

14. እኔም ቀኝ እጅህ እንደምታድንህ፣በዚያን ጊዜ አረጋግጬ እቀበላለሁ።

15. “አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን፣‘ብሄሞት’ ተመልከት፤እንደ በሬ ሣር ይበላል፤

16. ብርታቱ ወገቡ ውስጥ፣ኀይሉም በሆዱ ጡንቻ ላይ ነው።

17. ጅራቱ እንደ ጥድ ዛፍ ይወዛወዛል፤የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው።

18. ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።

19. እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው።

20. ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ።

21. በውሃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር ይተኛል፤በረግረግ ስፍራ ደንገል መካከል ይደበቃል።

22. በውሃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤የወንዝ አኻያ ዛፎች ይሸፍኑታል።

23. ወንዙ በኀይል ቢጐርፍም፣ አይደነግጥም፤ዮርዳኖስ እስከ አፉ ቢሞላም፣ እርሱ ተረጋግቶ ይቀመጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 40