ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 22:21-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ተመችቶሽ በነበረ ጊዜ አስጠነቀቅሁሽ፤አንቺ ግን፣ ‘አልሰማም’ አልሽ፤ከትንሽነትሽ ጀምሮ መንገድሽ ይኸው ነበር፤ቃሌንም አልሰማሽም።

22. እረኞችሽ ሁሉ በነፋስ ይወሰዳሉ፤ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ከክፋትሽም ሁሉ የተነሣ፣ታፍሪያለሽ፤ ትዋረጂያለሽም።

23. አንቺ፣ ‘በሊባኖስ’ ውስጥ የምትኖሪ፣መኖሪያሽን በዝግባ ዛፍ የሠራሽ ሆይ፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣መከራ በላይሽ ሲመጣ ጩኸትሽ እንዴት ይሆን!

24. “በሕያውነቴ እምላለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር “የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የቀለበት ማኅተም ብትሆን እንኳ ኖሮ፣ አውልቄ እጥልሃለሁ፤

25. ሕይወትህን ለሚሿት፣ ለምትፈራቸው ለባቢሎናውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደናፆር አሳልፌ እሰጥሃለሁ።

26. አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት ወደ ሌላ አገር ወርውሬ እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ።

27. ልትመለሱባት ወደ ምትናፍቋት ምድር ከቶ አትመለሱም።”

28. ይህ ኢኮንያን የተባለ ሰው፣ የተናቀና የተሰበረ ገምቦ፣ማንም የማይፈልገው ዕቃ ነውን?እርሱና ልጆቹ ለምን ወደ ውጪ ተጣሉ?ወደማያውቁትስ ምድር ለምን ተወረወሩ?

29. ምድር ሆይ፤ አንቺ ምድር፣ አንቺ ምድር፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!

30. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 22