ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 48:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ሞዓብ፤የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።

2. ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል።መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ሰይፍም ያሳድድሻል።

3. ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!

4. ሞዓብ ትሰበራለች፤ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።

5. ክፉኛ እያለቀሱ፣ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ወደ ሖርናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።

6. ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ!በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ።

7. በድርጊታችሁና በብልጽግናችሁ ስለምትታመኑ፣እናንተም ትማረካላችሁ፣ካሞሽም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣በምርኮ ይወሰዳል።

8. በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና፣ሸለቆው ይጠፋል፤ዐምባውም ይፈርሳል።

9. በራ እንድታመልጥ፣ለሞዓብ ክንፍ ስጧት፤ከተሞቿም ምንም እስከማይኖርባቸው ድረስ፣ባድማ ይሆናሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 48