ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 50:34-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ነገር ግን ቤዛቸው ብርቱ ነው፤ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ለምድራቸው ዕረፍትን ለመስጠት፤ተግቶ ይሟገትላቸዋል፤በባቢሎን የሚኖሩትን ግን ዕረፍት ይነሣቸዋል።

35. “ሰይፍ በባቢሎናውያን ላይ መጣ!”ይላል እግዚአብሔር፤“በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ፤በባለ ሥልጣኖቿና በጥበበኞቿም ላይ ተመዘዘ!

36. ሰይፍ በሐሰተኞች ነቢያቷ ላይ መጣ!እነርሱም ሞኞች ይሆናሉ፤ሰይፍ በጦረኞቿ ላይ ተመዘዘ፤እነርሱም ይሸበራሉ።

37. ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ!እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ!ለዝርፊያም ይሆናሉ።

38. ድርቅ በውሆቿ ላይ መጣ!እነሆ፤ ይደርቃሉ፤ምድሪቱ በፍርሀት በሚሸበሩ አማልክት፣በጣዖትም ብዛት ተሞልታለችና።

39. “ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣የጒጒትም ማደሪያ ትሆናለች፤ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም።

40. እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፤በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀራቸው”ይላል እግዚአብሔር፤“እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፣የሚቀመጥባትም አይገኝም።

41. “እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል።

42. ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተማል፤ ያስገመግማል።አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 50