ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 9:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቶአል፤ እንዲህም ይላል፤‘ምንኛ ወደቅን!ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው!ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”

20. እናንት ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።

21. ሞት በመስኮቶቻችን ገብቶአል፤ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቆአል፤ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዶአል።

22. እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የሰዎች ሬሳ፣በሜዳ እንደተጣለ ጒድፍ፣ማንም እንደማይሰበስበው፣ከዐጫጅ ኋላ እንደተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”

23. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤

24. የሚመካ ግን፣እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ በማወቁና፣በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣እደሰታለሁና፤”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 9