ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 15:29-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዛ በመቅረብ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ትሰጣለች።

30. ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለፈሳሽዋ ርኵሰት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰር ይላታል።

31. “ ‘በመካከላቸው ያለችውን ማደሪያዬን እንዳያረክሱና በርኵሰታቸው እንዳይሞቱ፣ እስራኤላውያንን ከሚያረክሳቸው ነገር ለዩአቸው።’ ”

32. ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን፣ ዘሩም በመፍሰሱ ርኩስ የሆነውን ሰው ሁሉ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 15