ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 26:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ ‘ትሰግዱላቸው ዘንድ ጣዖታትን አታብጁ፤ ምስል ወይም የማምለኪያ ዐምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

2. “ ‘ሰንበታቴን ጠብቁ፤ መቅደሴን አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

3. “ ‘በሥርዐቴ ብትሄዱ፤ ትእዛዜንም በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣

4. ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድሪቱ እህልዋን፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ።

5. የምትወቁት እህል፣ የወይን ዘለላ እስከምትቈርጡበት ጊዜ፣ የምትቈርጡትም የወይን ዘለላ፣ እህል እስከምትዘሩበት ጊዜ ያደርሷችኋል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ በጸጥታ ትኖራላችሁ።

6. “ ‘በምድሪቱ ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ትተኛላችሁ፤ ማንም አያስፈራችሁም። ክፉ አራዊትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።

7. ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።

8. ከእናንተ አምስቱ መቶውን፣ መቶውም ዐሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።

9. “ ‘ፊቴን ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ እንድታፈሩና እንድትበዙም አደርጋችኋለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 26