ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 1:34-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ከምናሴ ዝርያዎች፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

35. ከምናሴ ነገድ የተቈጠሩትም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።

36. ከብንያም ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ፤

37. ከብንያም ነገድ የተቈጠሩትም ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 1