ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 12:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ነበርና ባገባት ኢትዮጵያዊት ምክንያት ማርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር።

2. እነርሱም፣ “ለመሆኑ እግዚአብሔር (ያህዌ) የተናገረው በሙሴ አማካይነት ብቻ ነውን? በእኛስ አልተናገረም?” ተባባሉ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ይህን ሰማ።

3. ሙሴ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበር።

4. ወዲያው እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን፣ “ሦስታችሁም ውጡና ወደ መገናኛው ድንኳን ኑ” አላቸው፤ ሦስቱም ወጥተው ሄዱ።

5. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመና ዐምድ ወረደ፤ በድንኳኑም ደጃፍ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፤ ሁለቱም ወደ እርሱ በቀረቡ ጊዜ፣

6. እንዲህ አላቸው፤ “ቃሌን አድምጡ፤“የእግዚአብሔር (ያህዌ) ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር፣በራእይ እገለጥለታለሁ፤በሕልምም እናገረዋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 12