ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 16:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የእስራኤል አምላክ (ኤሎሂም) እናንተን ከቀሩት እስራኤላውያን ማኅበረሰብ መለየቱና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ማደሪያ አገልግሎት እንድትፈጽሙ ወደ ራሱ ማቅረቡ፣ እንድታገለግሏቸውም በማኅበረ ሰቡ ፊት እንድትቆሙ ማድረጉ አይበቃችሁምን?

10. አንተንና ከአንተም ጋር ወገኖችህ የሆኑትን ሌዋውያንን ሁሉ ወደ ራሱ አቅርቧችኋል፤ እናንተ ግን የክህነቱንም ሥራ ደርባችሁ ለመያዝ ይኸው ትሯሯጣላችሁ።

11. አንተና ተከታዮችህ ሁሉ አባሪ ተባባሪ ሆናችሁ የተነሣችሁት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ነው፤ ለመሆኑ ታጒረመርሙበት ዘንድ አሮን ማነው?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 16