ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 21:30-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. “እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ተደመሰሰች፤እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”

31. ስለዚህም እስራኤል በአሞራውያን ምድር ተቀመጠ።

32. ሙሴ ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ከላከ በኋላ እስራኤላውያን በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አባረሩአቸው።

33. ከዚያም ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ በመያዝ ሄዱ፤ የባሳን ንጉሥ ዐግና መላ ሰራዊቱም ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥሟቸው ወጡ።

34. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋር በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በእርሱም ላይ አድርግበት” አለው።

35. ስለዚህም እስራኤላውያን ዐግን ከልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋር አንድም ሳይቀሩ ሁሉንም ፈጇቸው፤ ምድሩንም ወረሱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 21