ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 25:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤላውያን በሰጢም በነበሩበት ጊዜ ወንዶቹ ከሞዓብ ሴቶች ጋር ማመንዘር ጀመሩ።

2. እነዚህም ሴቶች ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ሕዝቡን ጋበዙ፤ ሕዝቡም መሥዋዕቱን በላ፤ ለአማልክቱም ሰገደ።

3. ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን በኣል በማምለክ ተባበረ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ቍጣ በላዩ ነደደ።

4. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “አስፈሪው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ ፀሓይ ላይ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ስቀላቸው” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 25