ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 26:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤

2. “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከየቤተ ሰቡ ቊጠሩ።”

3. ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤

4. “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤

5. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤በፈለስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤

6. በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤

7. እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

8. የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣

9. የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።

10. ሁለት መቶ አምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከእርሱ ጋር ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 26