ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 28:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸውን ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ።

28. ከእያንዳንዱም ወይፈን ጋር ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፉ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራው በግ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቀርባል፤

29. ከሰባቱም የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፉ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቅረብ።

30. በተጨማሪም ማስተስረያ እንዲሆንላችሁ አንድ ተባዕት ፍየል አቅርቡ።

31. ከእህል ቊርባኑ ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በተጨማሪ እነዚህን ከመጠጥ ቊርባናቸው ጋር አቅርቡ። እንስሳቱም እንከን የሌላቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 28