ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 31:30-41 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ደግሞ ከሰውም ይሁን ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ፣ ከፍየል ወይም ከሌሎች እንስሳት ከየአምሳው አንዳንድ መርጠህ፣ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ስጣቸው።”

31. ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።

32. ወታደሮቹ ማርከው ከወሰዱለት ምርኮ ውስጥ የቀረው ይህ ነበር፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በግ፣

33. ሰባ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብት፣

34. ሥልሳ አንድ ሺህ አህያ

35. ወንድ ያላወቁ ሠላሳ ሁለት ሺህ ሴቶች።

36. በጦርነቱ ላይ የነበሩት ወታደሮች እኩሌታ ድርሻ ይህ ነበር፤ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በግ፤

37. ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠ ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበር።

38. ሠላሳ ስድስት ሺህ የቀንድ ከብት፣ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሰባ ሁለት ነበር።

39. ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ አህያ፣ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሥልሳ አንድ ነበር።

40. ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰው፤ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሠላሳ ሁለት ነበር።

41. ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የሆነውን ግብር ለአልዓዛር ሰጠው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 31