ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 31:40-47 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

40. ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰው፤ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሠላሳ ሁለት ነበር።

41. ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የሆነውን ግብር ለአልዓዛር ሰጠው።

42. ሙሴ ከዘመቱት ሰዎች የለየው የእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ማለትም፣

43. የማኅበረ ሰቡ ድርሻ ይህ ነበር፤ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በግ፣

44. ሠላሳ ስድስት ሺህ የቀንድ ከብት፣

45. ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ አህያ፣

46. ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰው።

47. ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ላይ፣ ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ከየአምሳው ሰውና እንስሳ አንዳንድ መርጦ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጣቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 31