ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 33:34-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ከዮጥባታ ተነሥተው በዔብሮና ሰፈሩ።

35. ከዔብሮና ተነሥተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።

36. ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በጺን ምድረ በዳ ባለችው በቃዴስ ሰፈሩ።

37. ከቃዴስ ተነሥተው በኤዶም ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።

38. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

39. አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 33