ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 4:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤

2. “ከሌዋውያን ወገን የቀዓት ዘር የሆኑትን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቊጠሩ።

3. እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ አምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠሩ።

4. “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የቀዓታውያን ሥራ ንዋየ ቅዱሳቱን መጠበቅ ነው።

5. ሰፈሩ ሲነሳ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚከልለውን መጋረጃ ያውርዱ፤ የምስክሩንም ታቦት ይጠቅልሉበት፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 4