እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።