እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የፍደሱር ልጅ ገማልኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።