ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 32:24-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድመቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ፤የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝምእሰድባቸዋለሁ።

25. ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ቤታቸውም ውስጥ ድንጋጤ ይነግሣል፤ጐልማሳውና ልጃገረዷ፣ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ።

26. እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውንአጠፋለሁ አልሁ፤

27. ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፣‘ድል ያደረገችው እጃችን እንጂ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፣’ ”የጠላትን መነሣሣት ሠጋሁ።

28. አእምሮ የጐደላቸው፣ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው።

29. አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡ፣መጨረሻቸውም ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነበር።

30. መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ካልተዋቸው በቀር፣አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል?ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደርጋሉ?

31. የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም።

32. ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው።

33. ወይናቸው የእባብ መርዝ፣የመራዥ እባብም መርዝ ነው።

34. “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 32